ለሚነሶታ ጥሩ ሁኔታ ለወደፊቱ እናዘጋጅ

ለሚነሶታ ጥሩ ሁኔታ ለወደፊቱ እናዘጋጅ
ማህበራችን የኮንትረት ውል ለማካሄድ የሚያስፈልጉ መመሪያወች
ከ7000 በላይ የጽዳት ሠራተኞች፣ የጥበቃ ኃላፊዎች፣ የአይሮፕላን ጣቢያ የአገልግሎት ሠራተኞችና የችርቻሮ
ጽዳት ሠራተኞች ከማህበራችን ጋር ውል ያደረጉት ካምፓኒዎች የሥራ ሁኔታ እንዲሻሻል በጋራ ቆመዋል።
የምንቆመው ለራሳችን ብቻ ሳይሆን 1% የሆኑት አሳሪዎች ዋናው የኢክኖሚ መስረት እንዲሆኑ ጫና
ከሚፈጠርባችው አብረውን ለሚሠሩት ሠራተኞችም ጭምር ነው። የ1%ቶቹን የድህነት መንገድ ወይስ
የተሻለች ሚነሶታን ለመፍጠር ሁኔታዎችን እናመቻቻለን? ብዙዎቻችን በሚቀጥሉት ሳምንታት ድርድር
አዲስ ውል ማህበሩ እንዲያደርግ እንቅስቃሴ እንደርጋለን።ለተወሰኑ ወራት ማህበሩ ከድረገቸው
ውይይት በመነሳት የሚከተሉትን የድርድር መመሪያዎች ተዘጋጅቷል።
1) ቤተሰቦቻችንን ከድህነት የሚያወጣ ክፍያ መጠየቅ
ቤተሰቦችን ሊደግፍ የሚችል ደመወዝ፣
የእራፍትና የበዓል ቀናት እንዲሻሻሉ መጠየቅ፣
የእራፍት ጊዜ እንዲረጋገጥ ማድረግ፣
የጡረታና የሕይወት እንሹረንስ እንዲረጋገጥ ማድረግ፣
የሚስጥር ጠቋሚዎች (Watchdog) በጀት ያለአግባብ ደሞዝና ሰዓት መስረቅ እንዳይደረግ
የመኪና ማቆሚያ ተመላሽ የሚድረገው ገንዘብ ተመላሽ መሆኑን መቆጣጠር፣
ገንዘብ በአግባቡ በአካውንት ውስጥ መግበቱን መቆጣጠር፣ ተመላሽ ለሚሆኑት ቼኮችና ትክክለኛ ያልሆኑ ቼኮችን በሚመለከት አስፈለጊውን ክትትል ማድረግ፣
ከ8 ሰዓት በላይ ለተሠራው የተጫማሪ ሰዓት ክፍያ መከፈሉን መቆጣጠርና ችግር ሲፈጠርም ተከታትሎ ማስፈጸም።
2) ሊቆረጥ የማይችል ጥሩ የጤና አገልግሎት
ብዙ ክፍያ የማይድረግበት የጤና፣ የጥርስና የዓይን እንሹረንስ እንዲኖር መከራከር፣
የጤና አገልግሎት ለሠራተኛው ለቤተሰቦቹ እንዲያገኙ መከራከር ፣
በየዓመቱ ብዙ የሕመም ቀናት እንዲገኝ መከራከር፣
የአጭር ጊዜ የአካል ጉድለት ሲደርስና በወልድ ጊዜ 2/3 ኛው ከክፍያችን እንዲከፈል ማድረግ።
3) የሙሉ ሰዓት ክፍያ ዋስትና እንዲኖር ማድረግ
ሁሉም ሥራዎች የማህበራችን አባል የሆኑ ሠራተኞች በሚሰሩበት ቦታ የሙሉ ሰዓት ወይም የ 8 ሰዓት እንዲሆን ማድረግ፣
ማህበራችን ሥራ ሲያጣ ወይም መ/ቤቱ ወደ ሌላ ኮንትራት ሲፈጸም ወይም ሠራተኞችን ወደ ሌላ ቦታ ቢያንቀሰቅስ ከፍተኛ መከለከል ማድረግ፣
ሕግ ወጥ የሆነ የሥራ ጫና በሠራተኛው ላይ ቢፈጸም ማህበሩ መከለከል ያደርጋል፣
የሠራተኛውን ደህንነት ለመጠበቅ የተሻለ ሥልጣና የመሰሪያዎች አጠቃቀም እንዲደረግ መጠየቅ፣
የሥራ ሁኔታን ለማሻሻል የሚረዳ የትምህርት ገንዘብ እንዲሰጥ መጠየቅ፣
ለጥበቃ ኃላፊዎች ግልጽ መመሪያ ከአስተዳደር ክፍል እንዲሰጣቸው መጠየቅ፣
ለጊዜያዊ ሠራተኞች አስፈላጊውን መከለከል ማድረግ፣
ከሥራ የማገድ ወቅት ከ30 ቀናት በላይ እንዳይሆን መጠየቅ፣
ብዙ ጊዜ በሥራ የቆዩ ሠራተኞች መብታቸውን ማስጠበቅ፣ እንዲሁም ሠራተኞች ከሥራ ሲወገዱ መብታቸው እንዲጠበቅ ማድረግ።
4) ተደማጭነት በሥራ ቦታ እንዲኖር ማህበር አስፈለጊ ነው።
ቅሬታን ፈጣንና ያለአድልዎ ለማስመዝገብ ይረዳል፣
በመጋቢነት አገልግሎት ለሚሰጡት ክፍያ እንዲያገኙ ማድረግ፣ ሥልጣናና የሥራ ትውውቅ ለአዲስ ሠራተኞች እንዲሰጣቸው ማድረግ፣
ሠራተኞች ሊያውቁ በሚችሉበት ሁኔታ በሚገባቸው መልክ ከአሰሪው መ/ቤት ጋር ስለ ሕንጻዎችና ለተለየዩ መረጃዎች ትውውቅ እንዲያደርጉ ማድረግ።
5) ሕብረተሰቡን የሚረዳ እንቅስቃሴ ማድረግ
ብዙን ሕዝብ ጥቅም ሊያስጠብቅ በሚችለው ፖሊሲዎች የመሪነት ሚናን መጫወት፣
ወጣቶች በሕብረተሰቡ ውስጥ እንዳይቀጠሩ የሚያደርጉትን መሰናክሎችን ማስወገድ፣
1% የሚሆኑት ሀብታሞች ኢክኖሚው ከወደቀበት እንዲንሰራራ ለማድረግ ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑን መጠየቅ።
ጊዜው 1% የሚሆኑት ሀብታሞች የራሳቸውን ተመጣጣኝ የሆነ ሥራ የሚሠሩበት ወቅት ነው
ከላይ የተጠቀሱትን መመሪያዎች ተግባር እንዲዉሉ ማድረግ የግል እንድስትሪ ገቢእንዲጨምር ያደርጋል።$100 ሚሊዮን ገንዘብ ከኢክኖሚው ድቀት ላሽቆ በሚገኘው በሚነሶታ ድሃ ሕዝብ በዓመት እንዲጨምር ያደርጋል። ጊዜው የሚነሶታን የእድገት አቅጣጫ ለማስተካክል ኮንትራክተሮችና 1% የሚሆኑት ሀብታሞች የራሳቸውን አስፈላጊ ግዴታ የሚወጡበት ወቅት ነው።
ፌስ ቡክ ለይ በዚህ አድራሻ ያገኙናል
ወይም በዚህ ቁጥር ይደውሉ 1-855-26LOCAL ወይም የማህበራችን ቢሮ ይምጡ 706 1st Street North Mpls.

Did you like this? Share it:

Comments are closed.